Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩኒሴፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስትን የልማት እቅዶች በመረዳትና የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታውቋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ÷የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ ለሚሰራቸው የልማት ስራዎች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተተገበሩ ስላሉ የልማት ስራዎችና የሀገሪቱ እቅዶችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰራች መሆኗን ያነሱት ሚኒስትሯ ÷ይህንንም የጋራ ስራ የማጠናከር ፍላጎት መኖሩን ገልጸዋል፡፡

አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር ) በበኩላቸው÷ ዩኒሴፍ የኢትዮጵያን መንግስት የልማት እቅዶችና ፍለጎቶች በአግባቡ ይረዳል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ከነዚህ እቅድና ፍላጎቶች ጋራ የተጣጣመ ስራን ለማከናወን ፍላጎት እንዳላቸውም አስታውቀዋል፡፡

በህጻናትና እናቶች ፣ በድህነት ቅነሳ ፣ በጤናና ማህበራዊ ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማጠናከር እንሰራለን ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version