Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በትግራይ ክልል ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በትግራይ ክልል ጉብኝት እያደረጉ ነው።

አምባሳደሩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ በትግራይ ክልል ለሶስት ቀናት ጉብኝት እንደሚያደርጉ የህብረቱ መረጃ ያመላክታል።

በቆይታቸውም በክልሉ በነበረው ግጭት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version