Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአረብ ሊግ ጉባኤ በሳዑዲ አረቢያ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 32ኛው የአረብ ሊግ ጉባኤ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባኤው በእርስ በእርስ ጦርነት የምትታመሰው ሶሪያ ከ12 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጉባኤው ተሳትፋለች፡፡

ሶሪያን በመወከል ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ጉባኤውን ለመካፈል ጅዳ የተገኙ ሲሆን በአረብ ሊግ ጉባኤ አባል ሀገራት መሪዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ጉባኤውን ለመካፈል ጅዳ የከተሙ ሌላኛው መሪ መሆናቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version