Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ የነበሩ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች በቁጥጥር መዋላቸው ተገለጸ።

ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አስታውቀዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል ያሉ ሲሆን ፥ ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ማረሚያ ቤቱ ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ መዋሉን አስተባባሪው አክለዋል።

ታራሚዎቹ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ተገቢ የሆነ የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላልም ነው ያሉት።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version