Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 በ26ኛ ሳምንት ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ ጨዋታ በሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በጣለው ከባድ ዝናብ ሜዳው ጨዋታውን ማካሄድ እንደማይችል የጨዋታ አመራሮች አረጋግጠዋል።

በዚህም ምክንያት  ጨዋታው የተራዘመ ሲሆን÷ በቀጣይ በሚገለፀው ቀን መሰረት በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ማሳወቁን ከሊግ ካምፓኒው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version