Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ኢንቨስትመንት መሳብና ድጋፍ ማድረግን አላማው ያደረገ ፕሮጀክት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ኢንቨስትመንት መሳብን እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል ማድረግን አላማው ያደረገ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል፡፡

ፕሮጀክቱ ኦሲቢ ግሎባል እና ትሪፕል ላይን ከተሰኙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ጉዳዩ በቅርበት ከሚመለከታቸው ተቋማት እና አካላት ጋር እንደሚተገበር ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በተለይም በግብርና ማቀነባበሪያው የኢንቨስትመንት ዘርፍ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዕድል እና አማራጮችን ገብተው እንዲቃኙ የማድረግ እቅድ እንዳለው መገለጹን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version