Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዜጎች ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ይሆናሉ የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲጠቁሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዜጎች ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ይሆናሉ የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽን የተቋቋመበትን ዓላማ እና በሕዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት እና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዓላማ መሳካትም ዜጎች ተገቢውን ትብብር እና ተሳትፎ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በእስካሁኑ ሒደትም በኢሜል፣ ፖስታ፣ ስልክ እና በአካል ተገኝተው የውይይት አጀንዳዎችን ከሚያስገቡ ዜጎች የውይይት አጀንዳ ማሰባሰብ መጀመሩ ተጠቅሷል፡፡

ስለሆም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በስልክ ቁጥር 0111261196 /0975554500/፣ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 32623 እና በኢ-ሜይል አድራሻ ethiopianndc@gmail.com አጀንዳዎችን እንዲያቀርብ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በአካል ማቅረብ ለሚፈልጉም ሽሮ ሜዳ አካባቢ አሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና ጽህፈት ቤት በመገኘት ጉዳዮችን ማቅረብ እንደሚችሉ ተጠቁማል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version