Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማኅበራዊ ትሥሥር ገፆች የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዲዋጉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማኅበራዊ ትሥሥር ገፆች የተሳሳቱ መረጃዎችን እንዲዋጉ የአውሮፓ ኅብረት ጠየቀ፡፡

ኅብረቱ እንደ ጉግል፣ ሜታ፣ ማይክሮሶፍት፣ ቲክ ቶክ፣ እና ሌሎች ባለቤት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በፅሑፎች ፣ ፎቶዎች እና በሰው-ሰራሽ አስተውሎቶች አማካኝነት ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ የሚቀርቡ እና የሚሠራጩ አሳሳች መረጃዎች ላይ መለያ “ሌብል” በመለጠፍ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጠይቋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ቬራ ጆውሮቫ በብራስልስ በሰጡት ማሳሰቢያ÷ በተለይ አሁን አሁን በሰው-ሰራሽ አስተውሎቶች አሳሳች ይዘቶች እና ምስሎችን በሠከንዶች ውስጥ መፍጠር የተቻለበት ጊዜ ላይ መደረሱ የ”ሐሰት መረጃዎችን ለመዋጋት አዲስ ፈተና ሆኖ ብቅ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

በማኅበራዊ ትሥሥር ገፆቻቸው የሰው-ሰራሽ አስተውሎት የመፈለጊያ ማሽን ያካተቱት እንደ ማይክሮሶፍቱ ቢንግ እና እንደ ጉግሉ ባርድ “ቻት ቦት” ያሉት አገልግሎት አቅራቢዎች ተንኮል አዘል መልዕክቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥርዓቶችን መገንባት አለባቸውም ብለዋል።

የማኅበራዊ ትሥሥር ገፆች የሐሰት መረጃዎችን ለመዋጋት ከ27ቱ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት ጋር ሥምምነት መፈራረማቸውን የአሜሪካ ድምፅ አስታውሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version