Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኩላሊት ተግባር

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኩላሊት በርካታ ተግባር ያለው አንዱ የሰውነት ክፍል ነው፡፡

ይህ የሰውነት ክፍል ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ውስጥ በየቀኑ 20 ባልዲ ወይም 200 ሊትር ውሃ ያጣራል፣ ከሰውነት መርዛማ ነገሮች እና አሲድ በሽንት መልክ ያስወግዳል፣ የደም ግፊትን ይቆጣጠራል በተጨማሪም የሰውነትን የጨው መጠን ይቆጣጠራል፡፡

እንዲሁም በሰውነት ውስጥ ያለውን ካልሲየምና ፎስፌት በመቆጣጠር የአጥንት ጤንነት የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል በተጨማሪም የቀይ የደም ሴል መራባትን ይቆጣጠራል፡፡

የኩላሊት መታወክ ወይም መታመም ደግሞ በሰውነት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮች እና አሲድ በሽንት አማካኝነት ባለመወገዳቸው መታፈንን እና ለመተንፈስ መቸገርን ያመጣል ለደም ግፊት ሕመም ያጋልጣል፡፡

በተጨማሪም ሰውነት ቀይ የደም ሴልን በተገቢው መጠን እንዳያመርት ከማድረጉም በላይ አጥንት ጥንካሬ ያጣል፣ እንደተፈለገው መንቀሳቀስ እንዳይቻል ያደርጋል፡፡

የደም ግፊትን በማስተካከል ፣በምግብ ላይ ጨው በመቀነስ፣ስኳርንና ቅባትን (ኮሊስትሮል) በማስተካከል፣ሲጋራ ባለማጨስ፣ስፖርት በመስራት እና የሰውነት ክብደትን በማስተካከል ከኩላሊት በሽታ መጠበቅ ይቻላል፡፡

Exit mobile version