Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ማላዊ በአቻ ውጤት ተለያ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ማላዊ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር አከናውኗል፡፡
የሁለቱ አገራት ጨዋታ በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ እና ማላዊ ያደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት መጠናቀቁን የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ እና ማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች ከአፍሪካ ዋንጫው ውጪ ሲሆኑ÷ግብፅ እና ጊኒ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ በነሐሴ ወር መጨረሻ ኢትዮጵያ ከግብፅ ማላዊ ደግሞ ከጊኒ ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

 

Exit mobile version