Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፋኦ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ድጋፍ ማድረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን እና በኢትዮጵያ አለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ተወካይ ፋጡማ ሰይድ በተገኙበት የርክክብ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ከአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በድጋፍ የተገኙት ሶስቱ ሄሊኮፕተሮች የበረሃ አንበጣ አሰሳ ስራን በማቀላጠፍ እና በጥቂት ጊዜ ዉስጥ ሰፊ ቦታ የሚሸፍን አሰሳ በማድረግ ተባዩን በመከላከልና በመቆጣጠር በግብርና ምርት ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት ለመቀነስ ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

የበረሃ አንበጣን በመከላከል ረገድ ድርጅቱ ከዚህ በፊትም ለኢትዮጵያ ሁለት የኬሚካል መርጫ አዉሮፕላኖች እንዲሁም የኬሚካል፣ የተሸከርካሪዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን የሚታወስ ነው።

Exit mobile version