Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከቻይና ጄዲ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከቻይና ጄዲ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

 

ውይይቱ በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

 

ኩባንያው በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በኢ-ኮሜርስ፣ በዲጂታል የፋይናንስ ስርዓት እና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት እቅድ እንዳለው ገልጿል።

 

በተጨማሪም ኩባንያው የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች የመቃኘት እቅድ እንዳለው መግለጹን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version