Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ተስፋዬ ኡርጌቾ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው ተስፋዬ ኡርጌቾ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ከሚኖርበት አሜሪካ ለዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ተስፋዬ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲከታተል መቆየቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው
መረጃ ያመላክታል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ለመላው ቤተሰቦቹና ለስፖርት ቤተሰቡ መጽናናት ይመኛል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version