Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮቪድ 19 ስርጭት መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልዉዉጥና ዉይይት  ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 9፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ኮቪድ 19 ስርጭት መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልዉዉጥና ዉይይት ለ8ተኛ ጊዜ በቪዲዮ መካሄዱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህ የቪድዮ ውይይት ላይ በሲዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ዲሪባ ኩማ እና በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ  አምባሳደር አቶ ሚሊዮንን ጨምሮ በርካታ ምሁራንና ከፍተኛ አመራርና ባለሙያዎች ከኖርዊይ፣ ከጄኔቭ፣ ከለንደን፣ ከኒዮርክና ከሀገር ውስጥ መሳተፋቸው ተገልጿል።

በውይይቱም የኮቪድ 19 ስርጭት በመከላከል ረገድ የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን÷ በኦኮኖሚ የሚደርሰዉን ተፅዕኖ ከመቀነስ አንፃርም ሊሰሩ በሚገባቸዉ ሥራዎች ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።

ከዚያም ባለፈ የሀገራቸዉን ህዝብ በማስተባበርና በተቀናጀ መልኩ ዳሽ ቦርድ በማዘጋጀት ዉጤታማ ሥራ መሠራቱን በልምድ ልዉዉጡ ወቅት  ተገልጿል።

ህብረተሰቡም በቤት ከመቀመጥ ጀምሮ የብስክሌት ትራንስፖርት አገልግሎትን በመጠቀምና የእግር ጉዞን በማድረግ ዉጤማ ሥራ መስራቱን አንስተዋል።

በሌላ በኩል በሎጀስትክስ ዘርፍ የተሠማሩ አካላትን ደህንነት ማስጠበቅ ላይ ትኩረት በማድርግ የሠሩ መሆናቸዉን አዉስተዉ ይህም ለሀገራችን እጅግ ጠቃሚ ስለመሆኑ በዉይይቱ ተነስቷል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ  በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ከመጀመሪያዉ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የተደረገው የልምድ ልዉዉጥ  በትራንስፖርት ዘርፍ የኮቪድ 19 መከላከል ላይ መደረግ ስላለበት ተሞክሮ በርካታ ትምህርት የተወሰደበት በመሆኑና በርካታ ልምዶችም በኢትዮጵያ እየተተገበረሩ መሆኑን አብራርተዋል።

በቀጣይም በሚሠሩ ሥራዎች ላይ ዉይይቱ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው ÷በቀጣይ ሥራዎችን በቴክኖሎጅ ከማስደገፍ ጀምሮ መልካም ዕድሎችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሠራ  መናገራቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version