Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር ይካሄዳል።

ጨዋታው ምሽት 12፡10 ላይ በአቡጃ አቢዮላ ስታዲየም የሚደርግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ከቀናት በፊት አቡጃ የገቡ ሲሆን በሞሽድ አቢዮላ አለም ዓቀፍ ስታዲየም ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች አንድ አቻ በሆነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

Exit mobile version