Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ሃረርጌ መልካ በሎ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ መልካ በሎ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የ7 ሰዎች ህወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው በወረዳው ቶኩማ ጃላላ ካብራ ቀበሌ ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ 7 ሰዓት አካባቢ ነው፡፡

በአደጋውም ከሞቱት ሰባት ሰዎች በተጨማሪ በንብረት እና በቤት እንስሳቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በተፈጠረው ደራሽ ወንዝ ባስከተለው የተራራ መደርመስ ከሞቱት ሰዎች ውስጥም ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ነው የተባለው፡፡

Exit mobile version