Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህብረቱ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን አወደሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት ኢትይጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቴክኒክ ደረጃ የሚያደርጉትን ድርድር ለመቀጠል መስማማታቸውን አወደሱ።

ሊቀ መንበሩ ሃገራቱ በህዳሴው ግድ ዙሪያ ከሰሞኑ ያሳዩትን አቋም አድንቀው፥ የሶስትዮሽ ድርድሩን ለመቀጠል መስማማታቸውን እንደሚያበረታቱም ገልጸዋል።

ድርድሩም በትብብር መርህ፣ በመግባባትና በግልጽነት ሃገራቱ በፈረንጆቹ 2015 ለፈረሙት የትብብር መርህ ማዕቀፍ ተፈጻሚነት ይረዳልም ነው ያሉት።

ኮሚሽኑም ሶስቱ ሃገራት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጥ ስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

Exit mobile version