Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዝላታን ኢብራሂሞቪች የኤሲ ሚላን የቦርድ አባል ለመሆን መስማማቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድናዊው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች የጣሊያኑን ኤሲ ሚላን በቦርድ አባልነት ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል፡፡

እስከ 41 ዓመቱ ድረስ በኢንተርናሽናል እግር ኳስ የዘለቀው ግዙፉ አጥቂ ባለፈው ክረምት ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም ማግለሉ የሚታወስ ነው፡፡

ከእግር ኳሱ ከተገለለ በኋላ ከክለቡ ጋር ግንኙነቱን ያላቋረጠው ኢብራሂሞቪች ለሶሰተኛ ጊዜ ከኤሲ ሚላን ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ዝላታን በክለቡ በይፋ ስራ ለመጀመር በሚቀጥሉት ወራት ሪፖርት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version