Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሊዊስ ሱዋሬዝ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡራጓዊው አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በጥር የዝውውር መስኮት የአሜሪካውን ክለብ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል መስማማቱ ተገለፀ፡፡

ሱዋሬዝ በአንድ ዓመት የኮንትራት ውል ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር ለማምራት በቃል ደረጃ ሥምምነት ላይ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን÷ ይፋዊ ፊርማው በቅርቡ ይገለፃል ተብሏል፡፡

ሥምምነቱን ተከትሎም ሱዋሬዝ ከቀድሞው የባርሴሎና የቡድን አጋሩ ሊዮኔል ሜሲ ጋር በድጋሚ ይገናኛል ተብሏል፡፡

ሱዋሬዝ የአውሮፓ ቆይታውን በስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ብራዚሉ ግሬሚዮ ማቅናቱ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም በአያክስ፣ሊቨርፑል እና ባርሴሎና መጫዎቱ የሚታወስ ነው፡፡

Exit mobile version