Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከአኩሪ አተር ተረፈ ምርት ከ14 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከአኩሪ አተር ተረፈ ምርት የወጪ ንግድ 14 ነጥብ 19 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ከአኩሪ አተር ተረፈ ምርት የወጪ ንግድ 12 ነጥብ 38 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 14 ነጥብ 19 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተጠቅሷል፡፡

ለወጪ ንግድ የሚቀርበው የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት ለእንስሣት መኖ ግብዓትነት የሚውል መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕንድ እና አሜሪካም የአኩሪ አተር ተረፈ ምርት ቀዳሚ መዳረሻ ሀገራት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version