Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታላቁ የወንጪ ሩጫ በነገው ዕለት ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያዘጋጀው ውድድር ነገ ማለዳ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ በሆነው ወንጪ ሐይቅ ዙሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል።

የአዋቂዎች ውድድር 10 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን እንዲሁም ህፃናት የሚሳተፉበት የ1 ኪሎ ሜትር ውድድር እንደተዘጋጀ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሰቦቃ ተናግረዋል።

ታዋቂ አትሌሎችን ጨምሮ ከ300 በላይ አትሌቶች በውድድሩ የሚሳተፉ ሲሆን÷ ከ6 ሺህ በላይ የአካባቢው ማህበረሰብ የሩጫው ተካፋይ እንደሚሆን ተገልጿል።

ውድድሩን ለማከናወን አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለፁት አቶ ማቴዎስ ከታላቁ የወንጪ ሩጫ በተጨማሪ አካባቢውን ለስፖርት ቱሪዝም ምቹ መስህብ ለማድረግ የሚያስችሉ የመሮጫ ትራኮች፣ የፈረስ መጋለቢያዎችና ሌሎች የስፖርት ማዘውተሪያዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በሱራፌል ደረጄ

Exit mobile version