Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቤል ያለው የግብጹን ዜድ ኤፍ ሲ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ አቤል ያለው የግብጹን ዜድ ኤፍ ሲ መቀላቀሉን ክለቡ አስታውቋል፡፡

ከታችኛው ሊግ በማደግ የግብጽ ፕሪሚየር ሊግን እየመራ የሚገኘው ዜድ ኤፍ ሲ  የቅዱስ ጊዮርጊሱን የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈርም እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆቱ የሚታወስ ነው፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት የነበረው ተጫዋቹ ሊጠናቀቅ በተቃረበው የግብጽ የዝውውር መስኮት በይፋ ዜድ አፍ ሲን ተቀላቅሏል፡፡

በዚህም ከሳላሃዲን ሰዒድ ፣ ሽመልስ በቀለ ፣ ዑመድ ኡኩሪ እና ጋቶች ፓኖም በመቀጠል 5ኛው በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ኢትዮጵያዊ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡

Exit mobile version