አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በቻይና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በማህበረሰቡ ውስጥ መቆሙን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሃገሪቱ ትናንት ምንም ሰው በቫይረሱ መያዙ አልተመዘገበም ነው የተባለው፡፡
ረቡዕ ከቻይና ውጭ የመጣ አንድ ሰው ብቻ ነው በቫይረሱ መያዙ የተነገረው፡፡
በሌላ በኩል ግን አራት በሻንጋይ እና አንድ በሲችዋን ግዛት ከቻይና ውጭ የመጡ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ የታወቀ ሲሆን ይህም አጠቃላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 83ሺህ27 አድርሶታል ፡፡
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።