አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጎብኝዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ጎብኝዎቹም÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪኩን፣ ጀግንነቱን እና ጽናቱን በሚመጥን መልኩ ታሪክን ያሸጋገረ፣ ትውልድ የሚማርበት እና በወቅቱ የነበረውን አንድነት በሚገልጽ መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡