Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊያዋን አገኘች

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊያዋን አግኝታለች፡፡

ዛሬ በተደረገው ከ23 አመት በታች የነጠላ ወንዶች ብስክሌት ውድድር ኪያ ጀማል 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሞሪሺየስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።

በብስክሌት ኢትዮጵያ የመጨረሻ ውድድሯን በነገው እለት በድብልቅ ዘርፍ ታደርጋለች።

በሰለሞን በቀለ

Exit mobile version