Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሕገ-ወጥ መንገድ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 45 ሞተር ሳይክሎችና 95 ባጃጆች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቁ ነበር ያላቸውን 45 ሞተር ሳይክሎች እና 95 ባጃጆች መያዙን የሐረሪ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሞተር ሳይክሎች እና ባጃጆችም አስፈላጊውን ሠነድ ሳያሟሉ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳሱ እንደነበር የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version