Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚያስችል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በ14 የድጋፍ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን÷አሜሪካ በውሳኔው ላይ ድምጸ ተዓቅቦ ማድረጓ ተመላክቷል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ ከአፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት በተጨማሪ ሃማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ የሚጠይቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎም የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በአሜሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት መሰረዛቸውን  አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ውሳኔ ማዘኗን ገልጻለች ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

Exit mobile version