Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለውጡን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በሂርና ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ ሀገራዊ ለውጡንና ይዞት የመጣውን ውጤት የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የድጋፍ ሰልፉ ”ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ሰልፈኞቹ ጠንካራ ኢትዮጵያ በህብረብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ ትገነባለች! ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም! በምክክርና መደማመጥ ሰላምን እናጸናለን! የወል አቅማችንን በማጎልበት ኢኮኖሚያችንን በጽኑ መሰረት ላይ እንገነባለን! የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ አንድነትን የሚያጸኑ መፈክሮችን አሰምተዋል።

Exit mobile version