Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ንግድ ባንክ ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ብር ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮያ ንግድ ባንክ ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ብር ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አድርጓል፡፡

በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ያለአግባብ ከባንኩ የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት ከ10 ሺህ በላይ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል ብሏል፡፡

ከ121 ሺህ እስከ 95 ሺህ ብር ያለአግባብ ወስደው ያልመለሱ የግለሰቦችን ማንነት የሚያሳዩ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ስላስፈለገ ባንኩ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣውን መረጃ ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መረጃዎችን መመልከት ይችላሉ።
https://combanketh.et/customer-round-two

Exit mobile version