Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ 70 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛው ምዕራፍ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 70 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

በሣምንት 12 በረራዎችን በማድረግ በሚቀጥሉት አራት ወራት በሳዑዲ ዓረቢያ ሽሜሲ ማቆያ ማዕከል በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ ዛሬ በይፋ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዛሬው ዕለትም በሁለት በረራዎች 842 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

Exit mobile version