Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል ከ224 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ224 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ኢየሩስ መንግስቱ እንደገለጹት÷ በመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ በመሆን ላይ የሚገኙት ተማሪዎች በ454 ት/ቤቶች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ናቸው።

ከክልሉ መንግስት፣ ከመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ከህብረተሰቡ የተገኘ 151 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦ መርሐ ግብሩ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

መርሐ ግብሩ ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር በመቀነስ ትምህርታቸውን ተረጋግተው በመከታታል ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት መረጋገጥ አስተዋጽኦ እንዳለው ማንሳታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version