Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ለዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታ ፋይዳው የጎላ ነው-ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እንደ ሀገር ለጀመርነው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “በዛሬው ዕለት የፕሮግራሙን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ገምግመን በቀሪ ወራት መፈፀም ያለባቸው ተግባራትን ለይተናል” ብለዋል።

በዚህ መሰረትም በዓመቱ ለማሳካት የታቀዱ ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ከፕሮግራም ጽ/ቤት እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሚኒስትሮች እና የተቋማት ኃላፊዎች ጋር የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ነው ያሉት።

Exit mobile version