Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ የሚገኙ የብሪታንያ አምባሳደሮች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የብሪታንያ አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም አየር መንገዱ ጥቅም ላይ ያዋላቸውን የተለያዩ ዘመናዊ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎች መመልከታቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም በኢትዮጵያ እና ብሪታንያ እንዲሁም በመላው ዓለም የኢኮኖሚ እና የባህል ልውውጥን በማሳለጥ አገልግሎትቱን እያስፋፋ መሆኑን ገልጾ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው አስታውቋል፡፡

Exit mobile version