Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በ2017 በጀት ዓመት ክልላዊ የእቅድ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ2017 በጀት ዓመት ክልላዊ የእቅድ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ እየተወያየ ነው።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀጣዩ በጀት ዓመት ክልላዊ የልማትና መልካም አስተዳደር ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በሆሳዕና ከተማ እየመከረ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምክር ቤቱ በሁሉም ዘርፎች የበጀት ዓመቱ ግቦችና የትኩረት ነጥቦች ላይ በመወያየት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Exit mobile version