አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።
በዚህ መሰረትም ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተጠቁሟል።
ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎቱ አሳስቧል።