Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤጂንግ ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ነግሷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት መንገሱ ተነገረ።
 
ቤጂንግ በሚገኝ የጀምላ ማከፋፈያ የገበያ ስፋራ ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ነው ስጋቱ የነገሰው።
 
ሺንፋዲ በተሰኘው በዚህ የጀምላ ማከፋፈያ ውስጥ በስራ ላይ ለሚገኘው ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችም የቫይረሱ ምርመራ እየተደረጋለቸው እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ለቤጂንግ የሚስፈልገውን የአትክልና የስጋ ውጤት 80 በመቶው የሚያቀርበው ይህ ግዙፍ ገበያ ከቫይረሱ ጋር ስሙ ሊነሳ የቻለው በገበያ ስፍራው የሚሰሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ ነው።
 
ባለስልጣናት በገበያው ስፍራ ለውጭ ገበያ የሚቀርብን ሳልሞን የተሰኘው የአሳ አይነት ለመቆራረጥ በሚያገለግለው ስፋራ ላይ የኮሮና ቫይረሱ መገኘቱን አስታውቀዋል።
ይህንንም ተከትሎ በ100 የሚቆጠሩ የቻይና ፓሊሶች ሺንፋዲ ወደ ተባለው የገበያ ስፋር ሲያቀኑ ታይተዋል።
 
በገበያው በቅርብ ርቀት የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ውትራንስፖርት አገልግሎቶች መዘጋታቸው ነው የተነገረው።
Exit mobile version