Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤጂንግ 36 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይናዋ መዲና ቤጂንግ 36 አዲስ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

በከተማዋ ትናንት 36 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል ነው የተባለው።

ቫይረሱ በዋናነት በከተማዋ ከሚገኘው ትልቅ የመገበያያ ስፍራ ሳይዛመት አልቀረም ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎም ገበያው የተዘጋ ሲሆን፥ በአቅራቢያው በሚገኙ 11 አካባቢዎችም እገዳዎች ተጥለዋል።

ዛሬም በገበያው አቅራቢያ በሚገኙ 10 አካባቢዎች እገዳ ተጥሏል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል ሊያኦኒንግ ፣ ሄቤይ እና ሲቹዋን በተባሉ ግዛቶች ከቤጂንግ ጋር የተያያዘ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

ወደ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ በከተማዋም ሆነ በግዛቶቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተው አያውቁም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version