Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው ዓመት ከረጅም ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የተቀላቀለው ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ፡፡

የስፓንሰርሽፕ ስምምነቱ በትናትናው ዕለት የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ እና የክለቡ ፕሬዚደንት አቶ ኡብሳ ለገሰ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በትናትናው ዕለት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱ የገንዘብ እና የስፖርት ቁሳቁስ ያካተተ ሲሆን በስምምነቱ መሠረት ሰበታ ከተማ በማልያው ላይ የሜታ አቦ ቢራ ምርት ያስተዋውቃል ተብሏል።

በዚህም ሜታ አቦ ቢራ በአራት ዓመታት ውስጥ የሚከፈል ከ14 ሚሊየን ብር እና 4 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶችን በማስመጣት ለክለቡ እንሚያቀርብ ክለቡ አስታውቋል፡፡

Exit mobile version