Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 545 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 177 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም በከተማዋ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 545 መድረሱን ነው የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሪፓርት ያመለከተው።

በ24 ሰዓታት ውስጥ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ 7 የኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት 123 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል፡፡

Exit mobile version