Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሃጫሉን የገደለው ማንም ይሁን ማን ከህግ ማምለጥ እንደማይችል የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሃጫሉን የገደለው ማንም ይሁን ማን ከህግ ማምለጥ እንደማይችል የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

በተወዳጁና ጀግናው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ከባድ ሀዘን ነው የተሰማኝ ብለዋል ወይዘሮ አዳነች።

ሃጫሉ ቢሞትም መሞት የማይችል ስራ ሰርቷል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ማንም ይሁን ማን ሃጫሉን የገደለው ሰው ከህግ ማምለጥ እንደማይችል አረጋግጠዋል።

የእኩይ እና አስነዋሪ ስራውን ዋጋ በህግ ያገኛልም ብለዋል።

ለአርቲስት ሃጫሉ ቤተሰብና ለመላው ህዝብ ትዕግስትን፣ ብርታትና መጽናናትንም ተመኝተዋል።

Exit mobile version