Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእከል እየሆኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእከል መሆናቸው እየተነገረ ነው።

በዚህም ሜክሲኮ በዓለም በኮቪድ19 በተያዙ ሰዎች ብዛት አራተኛዋ ሃገር መሆኗ ተጠቁሟል።

በሀገሪቱ ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 35 ሺህ ዜጎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸው ተነግሯል።

አሜሪካ 3 ሚሊየን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ በከፍተኛ ደረጃ ቫይረሱ የተስፋፋባት ሀገር ሆናለች።

አሁን ላይ በሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቶ ከ135 ሺህ በላይ ዜጎችን ለህልፈት ዳርጓል።

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ያሳየው ለዘብተኝነት ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

Exit mobile version