Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን አልፏል፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ74 ሺህ በላይ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከአሜሪካ ቀጥሎ ብራዚል ሁለተኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ለኮሮና ቫይረስ በቂ ትኩረት አልሰጡም በሚል ተደጋጋሚ ትችት እያስተናገዱ ይገኛል፡፡

በሃገሪቱ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን ወደ 2 ሚሊየን ከፍ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አልፏል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

Exit mobile version