Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰው ላይ የተሞከረው ክትባት የሰዎችን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል አቅም ማሻሻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሰው ላይ ተሞክሮ መልካም ውጤት ማሳየቱ ተነገረ።

በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀው ይህ ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና የሰዎችን የበሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያሻሽል መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።

ክትባቱ ከፍ ባለ ሁኔታ ተስፋ ሰጭ ነው ያለው የቢቢሲ ዘገባ ቫይረሱን ለመከላከል በቂ መሆኑን ለማረጋገጥ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አስነብቧል፡፡

በመጀመሪያ ዙር በሰዎች ላይ በተካሄደው ሙከራ 1 ሺህ 77 ሰዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

መድሃኒቱ የሰዎችን የበሽታ ተከላካዩች (አንቲቦዲ) እና ነጭ የደም ህዋስ ማሳደጉ ተጠቁሟል።

ይህም ሰዎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው።

ብሪታኒያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትም ChAdOx1 nCoV-19 የተሰኘው ክትባት እንዲቀርብላቸው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታውቋል።

Exit mobile version