Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባንኩ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ከታክስ በፊት ያገኘው የትርፍ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 102 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም ከትርፍ ባሻገር የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 52 ነጥብ 92 ቢሊየን ብር ማድረስ መቻሉን ነው ያስታወቁት፡፡

ፕሬዚዳንቱ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በዘንድሮው አመት 9 ነጥብ 34 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን 45 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር አድርሷል፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ

Exit mobile version