Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍጋኒስታን በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ 17 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍጋኒስታን በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ በጥቂቱ 17 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

የቦምብ ፍንዳታው ሎጋር በተባለው ግዛት አስተዳደር ቢሮ ህንጻ አቅራቢያ በርካታ ሰዎች የበዓል ግብይት በሚፈጽሙበት ወቅት የተፈጸመ ነው ተብሏል፡፡

ፍንዳታው ታጣቂው ታሊባን ከአፍጋን መንግስት ጋር ለኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በተስማማበት ዋዜማ የተፈጸመ ነው፡፡

ዛሬ የሚጀምረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለሶስት ቀናት የሚቆይ ነበር፡፡

ታሊባን በጥቃቱ እጀ የለበትም ያለ ሲሆን በአንጻሩ አሸባሪው አይ ኤስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም፡፡

የግዛቲቱ አስተዳዳር ቃል አቀባይ ዴዳር ላዋንግ ጥቃቱ በአጥፍቶ ጠፊ የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም ብለዋል፡፡

የአፍጋን መንግስት እና ታጣቂው ታሊባን ለመድረስ ያሰቡት የተኩስ አቁም ስምምነት በእስረኞች ልውውጥ ሳቢያ እክል ገጥሞታል፡፡

የአሽረፍ ጋኒ አስተዳደር ታሊባን የያዛቸውን 1 ሺህ የመንግስት የደህንነት ሰዎች ከለቀቀ 5 ሺህ የታሊባን አባላትን ለመልቀቅ ተስማምተዋል፡፡

በመንግስት በኩል እስካሁን ከ4 ሺህ 400 በላይ የታሊባን አባላት የተለቀቁ ሲሆን ታሊባን በበኩሉ 1 ሺህ 5 የአፍጋን የፀጥታ አካላትን መልቀቁን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

Exit mobile version