Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

23 ሺህ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናትናው ዕለት 46 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 23 ሺህ ግራም ወርቅ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

23 ሺህ ግራም ወርቁ ናይጄሪያ ዜግነት ባለው ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቦሌ አየር መንገድ መያዙን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ግለሰቡ ወርቆቹን በህገወጥ መንገድ ወደ ዱባይ ይዞ ለመሄድ ሲሞክር ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

ይህን ህገ-ወጥ ተግባር በቁጥጥር ስር ለዋሉ የቦሌ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞችና የጸጥታ አካላት የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Exit mobile version