Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ምዝገባው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገ ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚጀመር መሆኑን ገልጿል፡፡

በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ለሚደረገው ምዝገባ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉም ቢሮው አሳስቧል፡፡
የግል የትምህርት ተቋማትም ከነገ ጀምሮ ምዝገባ ማካሄድ እንደሚችሉ መግለጹን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version