Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው እለት በ33 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡

ጋዜጠኛው በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋዜጠኝነት አገልግሏል፡፡

ጋዜጠኛ ፍቅሩ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበረ፡፡

የጋዜጠኛ ፍቕሩ ወልዱ የቀብር ስነ-ስርኣትም ዛሬ በመቐለ ከተማ ዓዲ ሹምድሑን ፅዮን ማርያም ቤተክርስትያን ተፈጽሟል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋዜጠኛ ፍቅሩ ወልዱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡

Exit mobile version