Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መሃመድ ሁሴን ሮብሌ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ መሃመድ ሁሴን ሮብሌን አዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው መረጡ።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሁሴን ሮብሌን የተመረጡት ባላቸው ዕውቀት፣ ልምድና ችሎታቸው መሆኑን ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ገልፀዋል።
መሃመድ ሁሴን ሮብሌ በሀገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው የመተማመኛ ድምጽ ካገኙ ከዚህ ቀደም ከስልጣናቸው የተነሱትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዓሊ ኻይርን የሚተኩ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዓሊ ኻይር ባሳለፍነው ሐምሌ ወር በሀገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው የመተማመኛ ድምጽ በማጣታቸው ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Exit mobile version