Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን ተሸኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን ሽኝት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን በዛሬው እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በተገኘችበት ነው የተሸኙት።
የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዚሁ ወቅት፥ አትሌቶቹ በስልጠና ያገኙትን ልምድ በጋራ ስራ እንዲያሳዩ አደራ በማለት በድል እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችና አሰልጣኞች በበኩላቸው ጥሩ ዝግጅት አድርገው ለውድድር መዘጋጀታቸውን መግለፃቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Exit mobile version